የኩታበር ወረዳ መረጃ - በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን

የኩታበር ወረዳ
ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና መልከዓ-ምድራዊ ፕሮፋይል

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ መረጃ

የኩታበር ወረዳ አጠቃላይ መረጃ

72,511 ሄ/ር ስፋት
114,457 ህዝብ (2016)
23 ቀበሌዎች
158 የህዝብ ጥግግት

1. የወረዳዉ ታሪካዊ አመሰራረት

ኩታበር ወረዳ በአማራ ክልል፣ በደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ ከሚገኙ 20 ወረዳዎችና 9 የከተማ አስተዳደር ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ከደሴ ከተማ በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት፣ ከአድስ አበባ በ421 ኪሎ ሜትር እና ከባህርዳር በ521 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ወረዳ ነው፡፡

የታሪክ አጭር መረጃ
  • ወረዳው በ1938 ዓ.ም ተቆርቆሯል
  • የመሰረቷት አቶ ብርሃነ ስላሴና ደጅ አዝማች በላይ አሊ ናቸው
  • ከመገኘቱ በፊት "መታሎበር" በመባል ትጠራ ነበር

2. የኩታበር ወረዳ መልከዓ-ምድራዊ ገጽታ

የአየር ንብረት ሁኔታ
  • ከፍተኛ ቦታ: 3,452 ሜትር
  • ዝቅተኛ ቦታ: 1,703 ሜትር
  • አማካይ የሙቀት መጠን: 15°C
  • አማካይ የዝናብ መጠን: 500-995 ሚሊ ሜትር
የመሬት አጠቃቀም
የመሬት አይነት መጠን (ሄ/ር) በመቶ
ደጋ 30,454.62 42%
ወይና-ደጋ 39,155.94 54%
ቆላ 2,900.44 4%
በደን የተሸፈነ 18,634 25.7%

3. የመሰረተ-ልማት አዉታሮች ሁኔታ

መብራት
  • ጠቅላላ የመብራት ሽፋን: 34.8%
  • 9 ቀበሌዎች መብራት ተጠቃሚ
መንገድ
  • ጠቅላላ የመንገድ ሽፋን: 26%
  • 4 ቀበሌዎች ክረምት-በጋ መንገድ ተጠቃሚ
  • 8 ቀበሌዎች የበጋ መንገድ ተጠቃሚ
  • 11 ቀበሌዎች ያለ መንገድ
የቴሌፎን አገልግሎት
  • አብዛኛዎቹ ቀበሌዎች የስልክ ተጠቃሚዎች ናቸው
  • 7 ቀበሌዎች የኔትወርክ መቆራረጥ ችግር አላቸው

4. የወረዳው ስነ-ህዝብ ሁኔታ

የህዝብ ብዛት በ2016 ዓ.ም
አካባቢ ወንድ ሴት ድምር
ከተማ 6,585 5,654 12,239
ገጠር 52,245 49,974 102,219
ጠቅላላ 58,830 55,627 114,457
የእድሜ አወቃቀር
እድሜ ምድብ ብዛት በመቶ
0-14 ዓመት 43,143 37.7%
15-64 ዓመት 63,049 55.1%
65+ ዓመት 6,295 5.5%
የሃይማኖት ስብጥር
  • ሙስሊም: 87.83%
  • ኦርቶዶክስ: 12.01%
  • ፕሮቴስታንት: 0.16%

5. ኢኮኖሚያዊ ልማት ዘርፍ

ግብርና ልማት

ግብርና በወረዳዉ ኢኮኖሚ የቀዳሚነቱን ደረጃ እንደያዘ የሚገኝ ሴክተር ነዉ፡፡

ዋና ዋና የሰብሎች ምርት (2015/16)
የሰብል አይነት የተዘራ መሬት (ሄ/ር) የተገኘ ምርት (ኩ/ል)
ጤፍ 2,188 3,537
ስንዴ 3,593 102,136
በቆሎ 465 6,189
ማሽላ 725 10,994
ባቄላ 652 9,780
እንስሳት ሀብት
የእንስሳት አይነት ብዛት በእንሰሳት መመጠኛ (TLU)
ቀንድ ከብት 82,315 57,620.5
በግ 84,005 8,400.5
ፍየል 79,835 7,983.5
ዶሮ 92,550 -

6. የቱሪዝም ሀብት ሁኔታ

ጥቃና ዩሃንስ ዋሻ

በ015 ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ከወረዳው ርዕሰ ከተማ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት በሰሜን ምእራብ የሚገኝ የተፈጥሮ ዋሻ ነው፡፡

ጀመሌ ደን

በ03 እና 09 ቀበሌ ድንበር የሚገኝ በጣም አስደሳች የሆነ ጥቅጥቅ ደን ሲሆን በተለያዩ የዱር እንሰሳትና አዕዋፋት የበለጸገ ነው፡፡

ልጎት አንባ

በ016 ቀበሌ የሚገኝ አንባ ሲሆን ከአጼ ቴወድሮስ እስከ ንጉስ ሚካኤል ዘመነ-መንግስት ድረስ ወታደራዊ ካምፕ ሆኖ አገልግሏል፡፡

መሆነኛ ተራራ

በ06 ቀበሌ የሚገኝ ከባህር ወለል በላይ በ3,000 ሜትር ከፍታ ያለው ባለ ግርማ ሞገስ ተራራ ነው፡፡

ንፋሳት እየሱስ ቤተ-ክርሲቲያን

በ08 ቀበሌ ውስጥ ከወረዳው በስተ-ሰሜን በ25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ነው፡፡

7. የተፈጥሮ ሀብት

የማእድን ሀብት
  • የደን ውጤቶች ማቀነባበሪያ: 735 ሄ/ር
  • ጥቁርና ነጭ ድንጋዮች ለግንባታ
  • ኮፐር፣ ብረት፣ ሲሊካሳንድ፣ ጃስፐር፣ ካኦሊን፣ አጌት፣ እብነበረድ ወዘተ.
የእጸዋት ሁኔታ

ዋንዛ፣ ዋርካ፣ ወይራ፣ ባህር-ዛፍ፣ የፈረንጅ ጽድ፣ የሀበሻ-ጽድ፣ ክትክታ፣ አጋም፣ ሾላ፣ ኮሶ፣ እንብስ፣ ከሴ፣ ሟጢስ፣ ዘግባ፣ ነጭሎ፣ እንቧጮ፣ ድከረንስ፣ ሽውሽዋ፣ ግራር፣ ወሌንስ፣ ጥቁር እንጨት፣ ወዘተ.

የዱር አራዊት ሁኔታ

ጭላዳ-ዝንጀሮ፣ ቀበሮ፣ ድኩላ፣ ሚዳቆ፣ ነብር፣ ጅብ፣ ጥርኝና የተለያዩ የአዕዋፍ ዝርያ በጥቂቱ ይገኛሉ፡፡

8. ማህበራዊ ልማት ዘርፍ

ጤና ጥበቃ ልማት
  • የጤና ተቋማት: በወረዳው ውስጥ የተለያዩ የጤና ተቋማት ይገኛሉ
  • የጤና ባለሙያዎች: በተለያየ ደረጃ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ያገለግላሉ
  • የህጻናት የጤና አገልግሎት ሽፋን: በወረዳው ውስጥ ከፍተኛ ሽፋን አለው
ትምህርትና ስልጠና ልማት
  • የተለያዩ ደረጃዎች ያላቸው የትምህርት ተቋማት ይገኛሉ
  • በየደረጃው ተገቢ የሆነ የመምህራን ምደባ አለ
  • የትምህርት ስራ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ እየተካሄደ ነው

መልዕክት

ይህ የኩታበር ወረዳ መረጃ በ2016 ዓ.ም በወረዳው ፕላንና ልማት የስራ ቡድን ተዘጋጅቷል፡፡ የወረዳው ልማት ለሁሉም ነዋሪዎች እኩል እድሎችን ለመፍጠር እና የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል የተደረገ ጥረት ነው፡፡

አድራሻችን
የኩታበር ወረዳን በጎግል ካርታ ያግኙ

ኩታበር ወረዳ በጎግል ካርታ

አድራሻ

ኩታበር ከተማ
ኩታበር ወረዳ
አማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ

ስልክ ቁጥር

+251-58-XXX-XXXX

ኢሜይል አድራሻ

municipality@kutabercity.gov.et